|
(ከፋትህ ታደለ ጋይንት)
መብቶች ከምንጫቸው በመነሳት በሁለት ይከፈላሉ፡፡ ሰው ሰራሽ መብቶችና ሰብአዊ መበቶች፡፡ሰው ሰራሽ መብቶች ሰዎች በሚፈጥሩት ውል(ኮንትራት)መሰረት አንድ ባለመብት ሌላው ባለግዴታ ሊሆን ይችላል፡፡
አበዳሪ በተበዳሪ ላይ መብት አለው፡፡ተበዳሪ ላበዳሪ የተበደረውን ገንዘብ የመመለስ ግዴታ አለው፡፡የአበዳሪው መብት# የተበዳሪው ግዴታ በሰዎች የእርስ በርስ ውል የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ሰብአዊ መብት በአንፃሩ ሰዎች ሰው ሆነው በመፈጠራቸወ ብቻ የሚኖራቸው መብቶች ናቸው፡፡ ሰብአዊ መብቶች እንደውል መብቶች ሰው ሰራሽ ሳይሆኑ ተፈጥሮአዊ ናቸው ፡፡
ሰብአዊ መብቶች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ የግልና የወል መብቶች (Group human right) ይባላሉ፡፡በተቃዋሚዎች “ በኢህአድግ SካŸM ካሉት መሰረታዊ ልዩነቶች አንዱ በወል (በቡድን) ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ነው፡፡
ኢህአድግ የግልና የወል ሰብአዊ መብቶች ተደጋግፈውና ተመጋግበው ሲከበሩ ነው ሙሉ ሰብአዊ መብት አክባሪ ስርዓት የሚመሰረተው ÃLM፡፡ }nªT>‹ የግል ሰብዓዊ መብቶች ይበቃል ይላK<፡፡ ወይም የግል ሰብዓዊ መብት እንጂ የወል መብት (Group human right ) የሚባል የለም ይላK<፡፡
ይሁንና የአናሳ ብሔረሰቦችና (minority group rights)# የአካባቢ ተወላጅ( indigenous people right )# የራስግ እድል በራስ የመወሰን መብት( the right to self –determination ) የሴቶች መብት (women’s rights )# ከመድሎ ነፃ የመሆን መብት (The right against discrimination) እና የዘር ማጥፋት ክልከላ (the right against genocide ) የጋራ (ቡድን)መብቶች ናቸው፡፡
በጋራ የመፀለይ እና አምላክን በቡድን የማምለክ የሃይማኖት ነፃነት (freedom of religion) ዋነኛው አካል ነው፡፡የአወንታዊ መድልዎ (affirmative action) መብት በተለይም ለአናሳብሄር ብሄረሰቦችና ለሴቶች እንዲሁም የባህልና የቋንቋ መብቶች በዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ህጐች በሚገባ የተደነገጉ መብቶች ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንዶቹ መብቶች ራሳቸው ችለው በዓለም አቀፍ ስምምነት ሰነድ (convention) ደረጃ የወጡ ናቸው፡፡ ለምላሌ የጾታ መድሎ ለማጥፋት የወጣ ስምምነት (CEDAW)# የአናሳ ብሔረሰቦች መብት (minority group) በተመለከተ የአካባቢ ተወላጅ ህዝቦች ጥበቃ የሚሰጡ (indigenous peoples) ስምምነቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡
u›”Ç”É ¨Ñ•‹ ›SካŸƒ ከላይ የተጠቀሱት ኢህአድግ የተቀበላቸው መብቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ (የተባበሩት መንግስታትም ጭምር) ዕውቅና የተሰጣቸው መብቶች ለኢትዮåያ አያስፈልጉም፡፡ወይም እነዚህ መብቶች በተቃዋሚዎች አስተሳሰብ የወል ወይም( የቡድን) መብቶች አይደሉም፡፡
ይህ Ndw በተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ }ጠቅሷል፡፡ወይም እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው መብቶች በመፍራት የወል መብት በግለሰበ መብት ይከበራል የሚል ስልታዊ የሃሳብ ማፈግፈግ አካሂደዋል፡፡
ስልታዊ ማፈግፈግ ባልከፋ#ነገር ግን ተቃዋሚዎች ለምንድን ነው የወል መብቶች (Group right) የሉም የሚK<ƒ? ሁለት ነገር ግን ተደጋጋፊ ምክንያቶች አሉት፡፡አንደኛው ነፋጣዊ ዘረኝነቱና ትምክህተኛ ተፈጥሮው የህዝቦች# የሴቶች# የአናሳ ብሄረሰቦች እንዲሁም በታሪክና በባህል ለተጐዱ ህዝቦችና ሴቶች የሚሰØ አዎንታዊ መድሎ (affirmative discrimination) ከተቀበለ ውድቀቱን ስለሚያረጋግጥ ነው፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ አንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎች አንድን ህዝብ ዘሩን ለመቀየጥ አልያም ለማጥፋት መሞከር አንድን ዘር የማጥፋት ክልከላ (the right against genocide) የወል (የቡድን) መብት መሆኑን ስለሚያውቁና የኢንተር ሀሞይን ባህሪያቸውን በወል መብቶች መከበር ስለሚደናቀፍ ነው፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ተቃዋሚ መሪዎች ሰለ ሰብአዊ መብት ተፈጥሮ ያላቸው እውቀት እጅግ አነስተኛ መሆኑ ነው፡፡ በቀላለና ግልጽ ቋንቋ ተቃዋሚዎች በዋነኛነት በፖለቲካው ሂደት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ "ህዝብን መፍራትና የህዝብን ልዓላዊነት ማክበር" መሆኑን ረስ}ª፡፡
የህዝብ ልዓላዊነት ማለት ደግሞ በራሱ የቡድን የህዝብ መብት መሆኑ አይገነዘቡም አልያም ከተገነዘቡ የማይቀበሉት ህልውናቸው አጠራጣሪ መሆኑን ስለሚረዱና ነው፡፡ ሰላም በወል የሚገኝ የሁሉም ሰው በጋራና በተናጠል ፍላጐት ነው፡ ሰላም የያንዳንዱ ሰው በግለሰብ ደረጃ መብት ቢሆንም ሰላም የሚገኘው ግን በተናጠል የግለሰቦች መብት መከበር አይደለም፡፡ ይልቁንስ ሰላም የህዝቦችና የአገሮች መብት የወል መብት ነው፡፡
በምንም ተአምር በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች የተደነገጉት የወል(ጥቅል) መብቶች የሉም ብሎ ሽምጥጥ አድርጐ መካድ አንድም ህዝብን የማጭበርበር ባህርይ# ሁለቱም የእውቀት ድህነት ቀንደኛ ምልክቶች ናቸው፡፡
በምን ሰሌት ነው የግለሰቦች መብቶች ከተከበሩ የአናሳ ብሄረሰቦች የወል መብት ለምሳሌ ቋንቋቸው በፍርድ ቤትና በት/ቤት የመጠቀም መብቶች የሚከበሩት? እንበዚህስ ቢሆን ኖሮ የኩቤክ ሰዎች (በቡድን) ከካናዳ ለመገንጠል ሪፈረንደም ማካሄድ ለምን ፈለጉ? በምን ምክንያታዊ ትንተና ነው የጾታ እኩልነት የግል መብት ተደርጐ የሚወሰደው? ሴቶች ጾታዊ በደል ደርሶባቸዋል ሲባል አንዲትም ሴት የወንዶች በላይ ተጠቃሚ የሆነች የለችም ለማለት አይደለም፡፡
ይልቁንስ ሴቶች በወል (በቡድን) በጾታቸው ምክንያት በታሪክ# በባህላዊ ወግና ልማድ ከወንድ በተለየ ተጐድተዋል ለማለት ነው፡፡ስለሆለም እኩልነታቸው ይረጋገጥ ብቻ ሳይሆን እኩልነታቸውን ለማረጋገጥ በወል ለሁሉም ሴቶች መብት ማረጋገጥና እንዲሁም የተለየ አዎንታዊ ድጋፍ/affirmative action/ ያስፈልጋቸዋል ÃvLM፡፡
የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ( the right to self-determination) በዓለም አቀፍ ህግ የተሰጠው ለግለሰቦች አይደለም የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየው ይህ መብት ቅኝ አገዛዝ (colonialist) የተያዙት ህዝቦች (በወል) ነጻ ለማውጣት የተሰጠ መብት ነው፡፡
’የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ ይውጡ’ ተብሎ በተባበሩት መንግስታት አዋጅ ሲነገር በመሰረቱ የህዝቦች መብት ለማክበር እንጂ የግለሰቦችን መብት ጉዳይ ቢሆንማ ቅኝ አገዛዝ ይሻላል ወይስ ነጻነት? በሚል ሪፈረንደም ማካሄድ በቀለለ፡፡ ቋንቋ# ባህል# ሀይማኖት እንዲሁም ንጹህ አካባቢ የማግኘት የመልማት# ከዘር ማጥፋት(genocide) የህግ ክልከላ የማግኘት መብቶች በመሰረቱ በግለሰብ መብትነት የሚታዩ አይደሉም፡፡
በካናዳ በመገንጠል ጉዳይ ላይ ሪፈረንደም የማካሄድ መብት ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡የኩቤክ ነዋሪዎች በርግጥ የግል መብቶቻቸው ስለሚጣሱ ሳይሆን በወል (የቡድን) መበቶቻቸው (ለምሳሌ የፈረንሳይኛ ቋንቋ በአስተዳደር መጠቀምና ማበልፀግን) በካናዳ አስተዳደር ስር አይቻልም የሚሉ ብዙ የኩቤክ ዜጐች ስላሉ ነው፡፡
ቋንቋና ባህልን የመሰሉ የወል መብቶች ከጥፋት ለማዳንና ለማበልጸግ በግለሰቦች ላይ የሚጣሉ ገደቦች አሉ፡፡መንግስታት ታሪካዊ ቅርሶች ለመጠበቅ ግለሰቦችን መብቶችን በህግ በመገደብ የተለየ እንክብባቤ ለባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ያደርጋሉ፡፡ በአንዳንድ ጉዳዮች የግለሰቦች መብት የወል (ቡድን) መብት ለማስከበር ሲባል ይገደባል፡፡
ቋንቋ በግለሰብ ብቻ ከጥፋት መታደግ ሆነ ማበልጸግ ስለማይቻል መነግስታት የተለየ ትኩረት በመስጠት ለመጠፋት የተቃረበ ቋንቋንና በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት በሚፈለግበት ጊዜ የተለየ የገንዘብና ተቋማዊ ድጋፍ ለቋንቋና ባህል ይሰጣል፡፡እነዚህ እርምጃዎች የወል መብቶች ለመጠበቅ ሲባል በአለም አቀፍ ህግም ቢሆን የሚደገፋ ህጋዊ በግለሰብ መብት ላይ የሚጣሉ ገደቦች ናቸው፡፡
የአካባቢ ንጽህና እና ተፈጥሮፈዊ ደኖች (right to environment) ደንን ጭምር የጋራ የወል ጥበቃ የሚያስፈልገው መብት ነው፡፡ አንድ ሰው (ግለሰብ) በአንድ ቦታ የአካባቢ (የአየር) ብክለት የሚያደርስ ተግባር መፈጸም የሚከለከለው ሌሎች ሰዎችን በወል ስለሚጐዳ ነው፡፡
የሀይማኖት መብት በሙሉነት የሚከበረው የአንድ ሀይማኖት አማኞች ሀይማኖታቸው የሚጠይቀውን ነገር በጋራ መፈጸም ሲችሉ ነው፡፡ በአብዛኛዎቹ ሀይማኖቶች መሰረት ፈጣሪያቸውን በጋራ ማምለክና መጸለይ ከፍተኛ ሀይማኖታዊ እሴት አለው፡፡
ይህ መብት በሚገባ የሚጠበቀው ግን እያንዳንዱ ሰው በግሉ በሚያደርገው እነቅስቃሴ ሳይሆነ ሁሉም ተከታይ በወል (በጋራ) የመጸለይና አምልኮውን የማካሄድ መብት በወል ሲጠበቅለት ነው፡፡በተቃዋሚዎች አባባል በየቤቱ በግሉ እያንዳንዱ ሰው መጸለይ ከቻለ በጋራ የወል የመጸለይ መብት መሰጠት አያስፈልግም የሚል አንድምታ አለው፡፡ይህ ከአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች አንጻር የሰበአዊ መብት ከፍተኛ ጥሰት ነው፡፡
ለሴቶች እኩልነት የተደረገው ትግል# የሀይማኖት ነጻነት ለመፍጠር የተከፈለው መስዋእትነት የህዝቦች ነጻነት (ከባርነትና ከቅኝ አገዛዝ) ለማስከበር የፈሰሰው ደም# የጥቁር ህዝቦች መብት በአሜሪካ ለማስከበር የወደቁት የነ ማርቲን ሉተር ኪንግ አይነት ታጋዮች ለግለሰበ መብት ብቻ ባይሆን ለአንድ የህዝብ ዘር ማለትም ለጥቁር ህዝቦች ነበር፡፡ በጾታቸው ሴቶች ለሆኑት ለተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች በወል# በቅኝ አገዛዝ ለነበሩትና በባሪያነት ለተገዙት ሁሉ# ለጥቁሮች በጋራ የወል መብት የማስጠበቂያ መብቶች ናቸው፡፡
}nªT> Ndw ›^TЋ ይህ የታሪክና የአለም አቀፍ ህግ ማስረጃዎች የት አደረÙቸውና ነው የግል ሰብአዊ መብት እንጂ የጋራ የሰብአዊ መብቶች የሉም ያሉት? በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የአይሁዶች ህዝቦች ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የአይሁዶች ዘር (gene)ለማጥፋት (genocide) ከተፈጸመ በºላ የአንድ ህዝብ ዘር ዓለም አቀፍ ደረጃ የህግ ጥበቃ ያስፈልገዋል ብሎ የተባበሩት መንግስታት የወሰነው ለምንድን ነው? የዘር ማጥፋት (genocide) ወንጀል በግለሰብ ላይ ሊፈጸም አይችልም፡፡
በግለሰበ ላይ የሚፈጸም ግድያ የዘር ማጥፋት(genocide) ሳይሆን ነፍስ ግድያ ወንጀል (homocide) ነው፡፡ የዘር ማጥፋት በአንድ ህዝብና ዘር ላይ የሚነጣጠር በመሆኑ ከዚህ ጥፋት ወይም(genocide) ነጻ መውጣት የሁሉም የሰው ዘሮች የጋራ መብት ነው፡፡ የዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ክልከላ ስምምነት(Genocide Convention) የሚሰጠው የህግ ጥበቃና ያጐናጸፊው መብት የግለሰብ ሰብአዊ መብት አይደለም፡፡ የሁሉም የሰው ዘር የጋራ ሰብአዊ መብት እንጂ፡፡
ታድያ K?KA‡ የግለሰብ እንጂ የጋራ ሰብአዊ መብት የለም የሚለው ለምን ይሆን? የግለሰቦች መብቶች ሲደመሩየወል (የጋራ) መብቶች ይሆናሉ፡፡ይህ ማለት የወል መብቶች የግለሰቦች መብቶች ድምር ብቻ አይደሉም (group rights are not summation of individuals rights) የሚለው አስተሳሰብ እንኳን በቅጡ ሊገነዘብ ያልቻለው የተቃዋሚዎች አመራር እንዴት አድርጐ ነወ የግለሰብና የወል መብቶች በሚገባ ልዩነታቸውና ተደጋጋፊነታቸው የሚያየው፡፡
እርግጥ ነው ቀስተደመና (rainbow) የቀለሞች ህብረት ውጤት ነው፡፡ ቀስተ ዳመና (rainbow) የተለያዩ ቀለሞች ድምር ውጤት ስለሆነ ከያንዳንዱ ግንጥል ቀለም የተለየ ነው፡፡ ከያንዳንዱ ቀለሞች ተለይቶ ሲታይም ይበልጥ ያማረ ሊሆን ይችላል በቀስተ ዳመና ውስጥ ያሉት ቀለሞች በመለያየት በናስቀምጣቸው ከቀስተ ዳመና እጅግ ያነሱ የተበጣጠሱ ቀለሞችን እናገኛለን፡፡
የግል ሰብአዊ መብቶች ቢደመሩም ከጋራ (የወል) ሰብአዊ መብቶች ያነሱ ናቸው፡፡ የግል ሰበአዊ መበቶች ቢከበሩም ቀሪ የሰብአዊ መብቶች ጥቅሞች አሉ፡፡ አዎንታዊ መድሎ (affirmative actions) ለሴቶችና በታሪክ ለተጐዱ ህዝቦች (minority groups and indigenous people) የሚሰጡ የልዩ ድጋፍ መብቶች ናቸው፡፡ በአለም አቀፍ ሆነ በአገራችን የልዩ ድጋፍ (affirmative action) በጋራ (በወል) ለሴቶችም ለአናሳ ህዝቦችም መስጠት ተገቢ ሰብአዊ መብት ተበሎ ታምኖበታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ለአካለ ጉዳተኞች አካል ጉዳተኛ በመሆናቸው በጋራ የተለየ ድጋፍና ተኩረት ይሰጣል፡፡
ይህም የሰብአዊ መበት ከሰብአዊነት የሚመነጭ ነው፡፡ በተቃዋሚዎች የሰብአዊ መብት ትንተና ለአካል ጉዳተኞች በጋራአካል ጉዳተኛ በመሆናቸው የተለየ እንክብካቤ ሰብአዊ መብትን አያከብርም ማለት ነው፡፡ ለምን ቢባል ለአካል ጉዳተኞች በመብትነት የሚሰጡ ድጋፎች የቡድን መብቶች ናቸው፡፡ የመልማት መብት (the right to development) የጋራ መብት እንጂ የግል መብት ተብሎ አይደለም የዓለም አቀፍ የህግ ድንጋጌ የሚታወቀው፡፡
ሰላምና ደህንነት የማግኘት መብት (the right to pace and security) ከዘር መድልዎ ከዘር መጥፋት ነፃ መሆን (the right against genocide) ልዩ ድጋፍ ለሴቶችና አናሳ ህዝቦች (affirmative action) የጾታ እኩልነት (right of equality ) ወዘተ በተቃዋሚዎች አይን ቦታና ዋጋ የላቸውም፡፡
በአጭሩ የወል መብቶች የተለየ መከበር ያላቸው መብቶች ናቸው፡፡ የወል መብት ያለመከበር ማለት በቀጥተኛ የግለሰበ መብት መጣስ ማለት ነው፡፡
ለአገራችንም የማያባራ ችግር ሊፈጠር የሚችለው የወል መብቶች ባለመከበራቸው ነው፡፡ የወል መበቶች ሆኑ የግለሰበ መበቶች በተደጋጋፊነት ሲከበሩ ብቻ ነው በአገሪቱ ሙሉነት ያለው ሰብአዊ መብት አክባሪ ስርአት መመስረት የሚቻለው፡፡
|