| የ2002 ምርጫ ወቅት ያልተወራረዱ |
|
|
|
| Written by solomon | |||
| Wednesday, 26 May 2010 15:54 | |||
|
ዛሬ የምሳ ስአታችን አላከበርንም፡፡ ከቀኑ 10 ስአት ነበር፡፡ የምርጫ ስራ ለጋዜጠኛ ጫናው የተለየ ይሆን ብየ ባስብም ማነፃፀሪያ ግን አጣሁለት፡፡ አንድም እንደማንኛውም ዜጋ ስለ ሀገር የሚያሳስበን በመሆኑ በተጨማሪም የስራ ግዴታችን ስለሚደራረብብ ስራ በዛብን ማለት እንችል ይሆን፡፡ የለም
የተወራረደ የተሳሳተ የምርጫ ወቅት መረጃ እሁድ ረፋድ አከባቢ አንድ ከፍተኛ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር ድምፅ የሚሰጡበት የምርጫ ጣቢያ ደረሱ። ከሌሎች እጩ ተወዳዳሪዎች ለየት ያለ አካህናቸው እዛው አከባቢ የነበርነው የጋዜጠኞችን ቀልብ በተለየ ሁኔታ ሳበው፡፡ ምንም እንኳን ቃለ ምልልስ ልናደርግላቸው ዝግጁ የነበርን ቢሆንም ከርቁ አመጣጣቸው የጋዜጠኞች ካሜራ ይበልጥ እንዲያነጣጥርባቸው አድርጎት ነበር፡፡ የምርጫ ቅስቀሳ ቆሞ ህዝብ በነፃነት ድምፅ በሚሰጥበት ስአት ሰላምታ የሚገለፀው የፓርቲያቸው የምርጫ ምልክት እያሳዩ ለምርጫ በተሰለፈው ሰው መሃል ሳይቀር ማለፋቸው አንዱ አስገራሚ ትእይንት ነበር፡፡ ሌላው በምርጫ ጣቢያ በተለይም ድምፅ መስጫ አከባቢ ስልካቸውን እያነጋገሩ በመንጎራደድ ያሳዩት ትርኢት ሌላው ቀልብ የሚሰብ ትእይንት ነበር፡፡
ያም ሆነ ይህ ጋዜጠኞች ስራቸን ስለማንረሳ ድምፃቸውን ሰጥተው ሲወጡ ምርጫ ሂደቱ እንዴት ነበር አልናቸው? የመድረክ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ገና ሲጀምሩ ‘ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ መሆኑን አለመሆኑ ተረጋግጧል’ በሚል የተማታ ቃል ሲጀምሩ የአፍ ወለምታ ይሆናል ብንልም ደግመው ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ አለመሆኑ ተረጋግጧል ብለው አረፉት፡፡ ስራችን መረጃ ለህዝብ ማቅረብ ነበርና በየፊናችን ኢንጂነር ግዛቸው ያሉትን ለህዝብ ጀሮና አይን አደረስነው፡፡የኢንጅነር ግዛቸው ገለፃ የምልአተ ህዝቡና ባለሙያዎቹ መነጋገሪያ ሆነ፡፡ከምርጫ ስነ ምግባር ህጉና ከኢትዮጵያ ምርጫ ህግ አንፃር ተገቢ አለመሆኑ የምርጫ ቦርድ የስራ ሃላፊዎችንና ዜጎችን በግብረ መልስ መልክ አፀፌታውን መለሱ፡፡
ኢንጅነር ግዛቸው ለመገናኛ ብዙሃን የምርጫ ሂደቱ ሳይጠናቀቅ ትላንት ከእኩለ ቀን በፊት የሰጠሁት አስተያየት ስህተት ነበረ በማለት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ፡፡ ኢንጅነር ግዛቸው እንደገለፁት የድምፅ መስጠቱ ሂደት ሳይጠናቀቅ ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ አለመሆኑ ተረጋግጧል ማለቴ ስህተት ነው፡፡ይኼ አስተያየት ከምርጫ ስነ ምግባር ህጉ ጋር የሚጋጭ ስለሆነም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡
ከሌሊት ጀምሮ የምርጫ ሂደቱን መከታተላቸውን የገለጹት ኢንጂነር ግዛቸው ሂደቱ ነፃ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡የህዝብን ድምፅ እንደሚያስከብሩና እንደሚያከብሩም ለኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት ቃለ ምልልስ አረጋግጡ፡፡ይህ ከላይ የገለፅኩት ሃሳብ በሙሉ በትክክል ፅፌው ከሆነ የጓደኛየ ነው፡፡ ታድያ ምንደነው? በሚል ትከሻየ ስበቅኩኝ፡፡ ነገሩ ካንተ የምሳ ሂሳብ መዝጋት ፍጥነት ጋር ስለሚቀራረብ ነው አለኝ፡፡ ነገሩ ገብቷቸው ፈጥነው በምርጫ ሂደቱ ላይ ለፈፀሙት ስህተት በማረማቸው ሊመሰገኑ ይገባል ሲለኝ እስከ መጨረሻው ያዝልቅላቸው በሚል ተስማምተን እኛም የእለቱ የምሳ ውይይታችን ማወራረጃ ውሃችን ተጎንጭተን ተለያየን፡፡
ሆኖም ከጓደኛየ ስለይ ሰሞኑን ከአንድ ሌላ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ጓደኛየ ቴፕ ተውሼ ያዳመጥኩት የመድረክ ፓርቲ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች የፕሬስ መግለጫ ትዝ አለኝ፡፡ እናም የሚከተለው ንኡስ ርእስ ሰጥቼ ለአንባቢያን ላካፍላቹህ ወደድክ፡፡ የፕሬስ መግለጫ የተሰጠው ለውጭ መገናኛ ብዚሃን ስለነበር ለመተርጎም ጊዜ ፈጀብኝ እንጂ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ መግለጫውን የሰጡት እስከ መገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ ማጠናቀቅያ እለት የመጨረሻ ቀን የነበረው ሃሙስ እለት ማታ ነበር፡፡ ለማንኛውም ይህ ሂሳብ እንደ ላይኛው ስላልተወራረደና በርከት ያለ አዳዲስ ነገሮች ስለያዘ ለማገናዘቢያነት ብንወስደው ይጠቅማል በሚል እንደሚከተለው አቅሪቤላቹህ አሎህ፡፡
ያልተወራረዱ የምርጫ ጊዜ የተሳሳቱ መረጃዎች ከዚህ በታች ቃል በቃል ፕሮፌሰር በየነ የተናገሩት በተቻለ መጠን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ቃል በቃል ለመተርጎም የሞከርኩት ነው፡፡ ሃሙስ እለት የወጣው የህዝብ ብዛት ኢህአዴግ ያለው መጠነ ሰፊ ድጋፍ ብዛት አያሳይም ወይ? ብሎ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኛ ጠየቀ፡፡ መላሹ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ምላሻቸው የሚከተለው ነበር፡፡
‘‘ኢህአዴግም ታዛቢዎችም ጭምር የተለየ አቋም ሊወስዱ እንደሚችሉ ብገምትም ለድጋፍ የወጡት ሰዎች ተከፍሏቸው ነው፡፡ አባል ተከፍሏቸዉ።ለዚህ ነዉ ሰልፍ የወጡት። የኢህአዴግ ዘዴ ስብሰባ በሚኖርበት ወቅት ለወጣቶች ይከፍላል።በአዲስ አበባ ጭምር ወጣቶችና ሴቶችን ስብሰባ እየጠራ ገንዘብ ይከፍላቸዋል…ስለዚህ ለወጣቶችና ለተቸገሩ ስራ አጦች ገንዘብ እንደተከፈላቸዉ በጣሙን አመንኩኝ።’’
ሌላ ጥያቄ ከሌላ ጋዜጠኛ ተሰነዘረ፡፡ ምርጫዉ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ባለቸዉ ከፍተኛ ድጋፍ እነሱ በከፍተኛ ድምፅ እናሸንፋለን ቢሊ ምን ስህተት አላቸዉ የሚል ነበር? የመድረክ የወቅቱ ተቀዳሚ ሊቀመንበር መለሱ፡፡ ‘‘እኔ ይህንን የምወስደዉ የተጥለቀለቀ ማጭበርበር እንጂ ድል ብዬ አልወስደዉም።’’
ሁለት እጅግ አስቸጋሪ ሂሳቦች ኢትዮጰያ ህዝብ ፊት ተደቅነዋል፡፡ የሚያወራርደው ህዝቡ ባይሆንም ህዝቡ ይቅርታ ሊያገኝባቸው የሚገቡ አስቸጋሪ ያልተወራረዱ የምርጫ ወቅት ሂሳቦች። ህዝቡ እየተከፈለህ ነው ሰልፍ የምትወጣው ለተባለው አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ዳግም እውነታውን አሳይቶ ይቅርታ ማስጠየቅ የሚችል መሆኑን በአንድ በኩል እንውሰድ፡፡ ሆኖም እነዚህ በትምህርት ትልልቅ ደረጃ እንደደረሱ የምናውቃቸው ሰዎች፡ ሰዎች ናቸውና ስሜታዊ አይሆኑም ተብሎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ እናም ሰከን ባሉበት በአሁኑ ወቅት እንደ ኢንጅነር ግዛቸው ሁሉ ፈጥነው ህዝቡን ይቅርታ በመጠየቅ ያልተወራረደ የምርጫ ወቅት ሂሳባቸውን ያወራርዳሉ ብለን መጠበቅም ተስፈኞች ስለማያሰኝ ሌላ አማራጭ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ለማንኛውም ህዝቡ የሚጠብቀው ያልተወራረዱ የምርጫን ሂደት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚመሩ የተሳሳቱ መረጃዎች መታረም ነውና አንድም እውነታውን አሳይቶ ይቅርታ ያስጠይቃል አልያም ለሰከኑት ፈጥነው ይቅርታ ለማለት ልቦና ይስጣቸው እያልክ መልካም የድህረ ምርጫ ዘመን ይሁንላቹህ እላሎህ፡፡ ሰላም፡፡
|
Add your comment
ADD
Comments, category: "amharic"
- የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ሕትመቱን አቋርጠው ተሰወሩ (4)
- እኛ ካላሸነፍን ምርጫው መጭበርበሩ ይታወቃል ሲሉ የአንድነት አመራሮች አስታወቁ (2)
- አቶ ስዬ አብርሃ መንታ መንገድ ላይ መቆማቸው ታወቀ (1)
- ከአፄው ስርዓት ጋር የሚመሳሰል የምርጫ ቅስቀሳ በተምቤን ተጀመረ (1)
- ኢትዮጵያ ግብረ-ሰዶም ባለመፍቀዷና ግልገል ጊቤን በማልማቷ ሁማን ራይትስ ዎች ከሰሰ፤ አቶ ገብሩ አስራትና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምንጭነት ተጠቅሰዋል (1)
- የኢ/ጉ/ገ/ ባለሥልጣን 6 ህገ ወጥ ነጋዴዎች ወደ ህግ ማቅረቡን አስታወቀ (1)











