RedBlueDark SmallMediumLarge NarrowWideFluid
ተቃዋሚዎች በምርጫው ውጤት ላይ እንፈርም ወይስ አንፈርም በሚል ተመካከሩ PDF Print E-mail
Written by solomon   
Saturday, 22 May 2010 07:43

በምርጫ 2002 የተሳተፉት የሀገራችን ተቃዋሚዎች በውጤቱ ላይ እንፈርም ወስይ አንፈርም በሚል ምክክር ማድረጋቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ። 

 

 

ተቃዋሚዎቹ ከምርጫው ቀደም ብሎ በነበሩት ሁለት ቀናት በኔዘርላንድ ኤምባሲ ተሰብስበው በውጤቱ ላይ ለመፈረም ወይም ላለመፈረም የጦፈ ክርክር ማድረጋቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል።

 

መድረክ የተባለ የተቋዋሚዎች ስብስብም የምርጫ ታዛቢዎቹ በውጤቱ ላይ እንዳይፈርሙ መመሪያ መስጠቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች አክለው ገልፀዋል።

 

ምንጮቻችን አክለው እንዳመለከቱት የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ሳይከናወን ገና ከወዲሁ በምርጫው ውጤት ላይ ለመፈረምና ላለመፈረም የተመካከሩት ተቃዋሚዎች፣ የምርጫው ውጤት በፀጋ ላለመቀበል ያላቸውን አዛማሚያና ፍላጐት ከወዲሁ የሚያመላክት እውነት ነው ብለዋል።

 

በተለይ መድረክ ያስተላለፈው መመሪያ የህዝብን ድምጽ ላለመቀበል ያለውን ፀረ-ዴሞክራሲ አቋም እንደሚያሳይ ምንጮቻችን አስረድተዋል። ይህም የምርጫ ስትራጂያዊ አንድ አካል መሆኑም ይታወቃል።

 

 

 

Add your comment

Your name:
Subject:
Comment: